መጽሐፍ ቅዱስ ነብያት እና ታሪካውያን የጻፉት የክርስቲያኖች እምነት መጽሓፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ለአይሁድና ክርስትና እምነት የእምነት መሰረት የሆኑ ትናንሽ መጽሐፍትን የያዘ አንድ ጥራዝ ነው። በተለምዶ "ብሉይ ኪዳን" በመባል የሚጠራውና በአይሁዳውያን በ24 እና በክርስቲያኖች በ39 መጽሐፍት የሚከፈለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በመጀመሪያ በአብዛኛው የተጻፈው በጥንታዊው የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን የተጻፉበት ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተወሰኑ መቶ አመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይነገራል። መጽሐፍ ቅዱስ ከመቶ 25% የአምላክ ንግግር፣ ከመቶ 25 % የነብያት ንግግር እና ከመቶ 50 % የታሪክ ጽሐፍያን ንግግር ይዟል።.